ፍጡር እንጂ ፈጣሪ ህየው ነው!!
መንግስት ባለፉት አንድ ዓመት ተኩል ለግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ከኢትዮጵያ ሀገር ምስረታ ትርክት እና እሴት ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል ላይ የቆየውን የኦሮሞ ብሄርተኝነት "ከኢትዮጵያዊነት" ጋር ለማስታረቅ የተከተለው መንገድ ጥድፍያ የተሞላበት እና መፈፀም ያለባቸውን ቅድሚየ ሁኔታዎች ሳያመቻች በግብታውነት ስለተጓዘ የኦሮሞ ህዝብንም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት ፈተና ላይ የሚጥል እንዲሁም ለመንግስት ህልውናም አደገኛ እንደሆነ ስንገልፅ ነበር። በተለያዩ ጊዜም መንግስት የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የተከተለው መንገድ መሪህ አልባ፣ግልፅነት እና ፍጥነት የጎደለው ስለሆነ በጊዜ ካልተስተካከል መንግስትን አጣብቂኝ ውስጥ በመክተት ለሀገር እና ለህዝቦች አንድነት መዘዙ ብዙ እንደሆነ ስናሳስብ ነበር።
ይህ አካሄድ በጊዜ ማስተካከያ ስላላገኘ ፦
1 መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከክልሉ ህዝብ እየተነጠለ እና ድጋፉ እየተመናመነ ይገኛል። በኦሮሞ ህዝብ (በተለይ በወጣቱ) ዘንድ የነበረው መነሳሳት እና ብሩህ ተስፋ ተሟጦ የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ።ለዚህ ደግሞ የጀዋር ጠባቂዎች ሊነሱ ነው በተባለ ጊዜ እና የሃጫሉን ሞት ተከትሎ በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች በሰዓታት እድሜ ውስጥ የተወሰዱ አንዳንድ እርምጃዎች ጥሩ ማሳያዎች ናቸው።
2 በክልሉ በኦሮሞ ህዝብ እና በሌሎች ብሄሮች መካከል ያለው አብሮነት መጠናከር በሚገባበት ወቅት ላይ እየተዳከመ በመሄድ በተለያዩ ጊዜ ግጭቶች ስከሰቱ ተስተውሏል።
3 በምዕራብ እና በደቡብ ኦሮሚያ በኦነግ ታጠቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች መካከል በነበረው ግጭት ምክንያት የአከባቢው ህዝብ ሰላም አጥቶ ስቃይ ውስጥ ነው የከረመው።
4 የኦሮሞ ህዝብ እና ሌሎች ህዝቦች ያደረጉትን መጠነ ሰፊ አመፅ እና በኢህአዲግ ውስጥ የተካሄደውን ትግል ተከትሎ የመጣውን ለውጥ ተስፋ በማድረግ ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ እና በለውጡ ከእስር የወጡ ብዙ የብሄሩ ፖለቲከኞች እስር ቤት ናቸው።
5 በአንፃራዊነት ሰላም የነበረው የምስራቅ እና ደቡባዊ ምስራቅ ኦሮሚያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ(በተለይ ያለፉት ሁለት ቀናት) አመፅ ውስጥ በመግባት በህብረተሰቡ እና በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት ተከስቶ ሰዎች ተገድለዋል። እሄ እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው።
6 በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ መካከል ከብሄሩ የወጡ እና ክልሉን እና የፌደራሉን ቁልፍ ስልጣን የተቆጣጠሩ እጅግ የቅርብ ጎደኛሞች መካከል ጭምር የሃሰብ ልዩነት ተፈጥሮ ግማሹ አጋጅ ፤ግማሹ ታጋጅ ፤ግማሹን ደግሞ የመንግስት መርህ አልባ እና ግልፅነት የጎደለው አካሄድ እየበላው በፊትም ሰው አልባ የነበረውን ድርጅት የሰው ምደረ በዳ አድርጎታል።
7 በተለይ በሸገር ተፈናቃይ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም መንግስት እየወሰዳቸው ያሉት አንዳንድ በጎ እርሚጃዎች በቂ ከለመሆናቸውም በላይ በጥናት ላይ ያልተመሰረቱ ፤ እርምጃዎቹ ከከተማው ነዋሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቢሆንም ውይይት ያልተደረገባቸው በመሆኑ በከተማው ነዋሪ ዘንድ ከፍተኛ ጥርጣሬን በመፍጠር የከተማው ነዋሪ በመንግስት ላይ ብቻም ሳይሆን በከተማዋ ያልተጠና ወደ ጎን መቦርቀቅ ምክንያት ሲፈናቀል በነበረው ገበሬ ፤ የኦሮሞ ቋንቋ እና ባህል ላይ ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዲኖረው አድርጎታል።
8 ሌሎች ብዙ ችግሮችን መዘርዘር ይቻላል።ነገር ግን የችግሮችን ዝርዝር እዚሁ ላይ ገታ ላድርግ እና ወደ መፍትሄው ላምራ።
መፍትሄው መንግስት በእውር ድንብር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በመግታት እና ቆም ብሎ በማሰብ
1 በሽግግር ጊዜ በተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎች መካከል ያለውን ልዩነት በእውነተኛ እና ግልፅ ውይይት እየፈቱ አኩራፍውን መቀነስ ለሽግግሩ ስኬት ወሳኝ መሆኑን መረዳት አንዱ ነው። ድርድሩ ሶስት እርከን ያሉት መሆን አለበት።
ሀ ,መጀመሪያ በጓደኛሞች እና በትግል አጋሮች መካከል መሆን አለበት። የውስጥ ድርድር ልንለው እንችላለን ።
ለ ,በመቀጠል እስር ቤት ካሉት እና በሰላማዊ መልኩ ከምንቀሳቀሱት የፖለቲካ ሃይሎች ጋር
ሐ, በመጨረሻም አንድ ላይ በመሆን በረሃ ያሉት መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ሰላማዊ የትግል ስልት እና ሰላማዊ ህይዎት እንዲመለሱ በሀቀኝነት መስራት ያስፈልጋል።
2 የኦሮሞን ጥያቄ ግልፅነት እና መሪህን በተከተለ መንገድ ብቻ ለመፍታት መሞከር
3 የ"ኦሮሞነት" እና የ"ኢትዮጵያውነት" ትርክትን ለማስታረቅ የሚደረገው ጥድፊያ የጭፍለቃ መልክ እንዳይዝ እና ቁጣ ቀስቅሶ በኦሮሞ ህዝብ እና በሌሎች ብሄሮች(በተለይ ከአማራ ህዝብ ጋር) መካከል ወደ ግጭት እንዳያመራ ከፍተኛ ጥንቃቄ መድረግ አለበት።
4 አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች አሁን ያለው መንግስት የኦሮሞ ብሄርተኝነትን በማጥፋት እና ክልሉን በማፍረስ የተለመደውን ኢትዮጵያዊነት ይገነባልናል ብለው የሚያልሙትን ቅዠት አይሉት ህልም በፍፁም ማቆም አለባቸው።ምክንያቱም የኦሮሞ ብሄርተኝነት በክልሉ እና ህገመንግስቱ ወይም በዚህ መንግስት የተፈጠረ ንፋስ አመጣሽ ብሄርተኝነት አይደለም።የኦሮሞ ብሄርተኝነት ክልሉን ፣ህገመንግስቱን እና እሄንን መንግስት ጭምር የፈጠረ በደም እና አጥንት የተገነባ ሃያል" ሃይል "ነው። ፍጡር እንጂ ፈጣሪ የማይጠፋ ህየው መሆኑን መረዳት እና የፈጣሪን ሃያልነት አምኖ መቀብል ለተጠናወታችሁ ደዌ ብቻኛው ፍቱን መደሃኒት ነው።
5 ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እና መፍትሄ ያላገኘው ችግር የኦሮሞ ህዝብ ብቻ አይደለም።እሱን እዚህ ላይ አላነሳሁም።ግን እነሱም መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል። በነሱ ላይ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
by dereje gerafa tulu 20/8/2020 EC
Post a Comment
if you have any questions let me know