ዛሬ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ፍጅት እየፈጸሙ ያሉት
የራሳችን ቀዲዳ ወነቤዎች ከአብሼ ገርባ ገዳዮች ጋር ተባብረው ነው።አብሼ ገርባ.....
ዘመኑ 1850-54 በሆሮ ኦዳ ቡሉቅ አባዱላ የነበሩት ገርባ ሁሩባ የስልጣን ዘመናቸውን ሳያጠናቅቁ ድንገት ህይወታቸው አለፈ።
.
በገዳ ህግ መሰረት የግድ ተሰባስበው መሪያቸውን ሊመርጡ ግድ ይል ነበር።በወቅቱ ደግሞ የጎጃም ወራሪዎች በተለያየ ግዜ ጥቃት እያደረሱ ዘረፋ እና ህይወት ያጠፉ ስለነበረ የሆሮ እና አከባቢውን ከጥቃት የሚመከላከለውን ሰራዊት የሚመራውን የገዳ ሀዩዎች ግዜ ወስደው ለመምረጥ በማሰብ ላይ ሳሉ አንድ በኦሮሞ ባህል ተደርጎ የማይታወቅ ድፍረት ተከሰተ።
.
የሟቹ አባ ዱላ ወንድ ልጅ በድንገት ተነስቶ "..ከዛሬ ጀምሮ አባዱላው እኔ ነኝ.."በማለት አዋጅ አስነግሮ ፈረሱ ላይ በመውጣት በአባቱ ይመሩ የነበሩትን ሰራዊቶች እንዲከተሉት ትእዛዝ አስተላለፈ።
.
በእርግጥም በወቅቱ በአስቸኳይ ወራሪዎቹን የሚመመክተው ጦር አዛዥ ያስልለገዋል። ይህን ችግር የገዳ አባቶች ቢያውቁትም ከጥንት ሲፈጸም የነበረውን የገዳ ስርአት ህግ በእነሱ ዘንመ ለማፍረስ ፈጽሞ አልፈቀዱምና የወጣቱን አብሼ ገርባ ሀሳብ ተቃወሙ።
.
ህዝቡም እየደረሰበት ባለው መገደል እና መዘረፍ እየባሰበት በመሄዱ ከሁለት ተከፈለ።
"...በአብሼ ገርባ መሪነት ወረራውን መመከት
አለብን.." በሚሉት በብዛት ወጣቶች በሆኑት እና "...ብንሞትም ህግ ሊጣስ አይገባም..." በሚሉ ሀይሎች ።
.
በመጨረሻም አብሼ ገርባ በ1855 በጉልበት አባ ዱላ ሆነ።የሚፈጸምባቸውን የጎጃም ወረራ እየመከተ አራት አመት እንደቆየ እንደ ገዳ ስርአት መልቀቅ ሲገባው እንቢኝ በማለት አሁንም አመጸ። እንቢታውን ቢያሰማም ባልተለመደ ሁኔታ የጎጃም ወራሪዎች ተጠናክረው ወረራቸውን ይፈጽሙነበር
.
በዚያን ዘመን ይመስለኛል ለወረራ ዘምቶ ያለመመለሱን መግለጽ የፈለገች ውሽማ እንዲህ ተቀኘች
.
.አመጣለሁ ብሎ ጆሮ ትልትል በሬ
ጮመን ገብቶ ቀረ የጎጃም ገበሬ
.
.
በማለት ሚስቲቱን ሸንቆጥ ያደረገችው።
.
ወደ አብሼ ስንመለስ ጀግንነቱን የመሰከሩለት ወራሪዎች አብሼ ገርባን በጦርነት አሸንፈው ያሻቸውን መፈጸም እንደማይችሉ ካረጋገጡ የሰነባበቱ ስለሆነ አንድ ሌላ ዘዴ በመያዝ ብቅ አሉ።
.
ቀዲዳ ወነቤ በሚባልና ከጎጃሞች ጋር በወገነ ሰው አመካኝነት "ካንተ ጋር የሰላም ስምምነት ማድረግ እንፈልጋለን..."በማለት በወርቅ የተለበጠ የፈረስ ልብስ ጌጥ በስጦታነት (መደለያ) ልከውለት ከራስ ደረሱ ጋር እንዲነጋገር በማድረግ እንደ ኦሮሞ ባህል መሰረት መሀላ ተደርጎ በጎጃም አና ኦሮሞ መካከል ሰላም የሰፈነ ለማስመሰል ተሞከረ።
.
ይህ የተፈጸመው መሀላ የእውነት እንዳልሆነ በወቅቱ ከአብሼ በታች የነበሩት አባዱላ ደበላ ገና እና ደጎ ሆሮ ሊያስረዱት ብዙ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።
.
በዚህ መልኩ ስምምነታቸውን ከፈጸሙ ቦለሃ ጎጃሞች አብሼ መዘናጋቱን በማረጋገጣቸው የሞርሞርን ወንዝ በመሻገር የጉድሩን እና ሆሮን ድንበር አልፈው ከአብሼገርባ መቀመጫ 20ኪ/ሜ ርቀት ካለችው ኮኮር ላይ ጦራቸውን አሰፈሩ።
.
ይህን ዘግይቶ የሰማው አብሼ አራት ሺህ የሚሆን ጦር ይዞ የጎጃም ጦር ወደl ሰፈረበት ሲያመራ ካሁን ቀደም ያደረጉት መሀላ በመካላቸው በመኖሩ አካሄዱ ለጦርነት አልበረም።
.
የጎጃም ጦር መሪ ወደ አረፉበት ቤት ለመግባት ሲል እንደ ኦሮሞ ባህል መሰረት ትጥቅን እንደታጠቁ መግባት ሰፉ በመሆኑ ትጥቁን ፈትቶ ደጅ በማስቀመጥ ለውይይት ወደ ውስጥ እንዳመራ ጭለማው ውስጥ ተደብቀው ይጠብቁት የነበሩት እላዩ ተረባርበው እግሮቹን እና እጆቹን አሰሩ።
.
በመቀጠልም አብሼ ገርባን መያዛቸውን የሚገልጸውን ነጋሪት ሲደልቁ ነበር የአብሼ ጦር የሆነውን የተረዱት።
.
በሁሉም አቅጣጫ በጎጃም ጦር መከበባቸውን ቢረዱም እጅን ለወራሪ መስጠት በደማቸውም አልነበረምና ተኩስ ከፈቱ።
.
ቀደም ሲል መግደያ ስፍራ በመያዝ አብሼን እና ሰራዊቱን ወጥመድ ውስጥ የከተተው የጎጃም ሀይል በመጨረሻ የአብሼን ተዋጊ ሀይል አሸነፉ።
.
በዚህም ውግያ አባዱላ ደበሎ ገናን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ተገደሉ፣ የአብሼ ገርባ ወንድምን አካሉን በአሰቃቂ ሁኔታ ቆራረጡት።
.
.
ይህ በየካቲት 13,1877 የተደረገው ጦርነት የኮኮር ሜዳ ውግያ ተብሎ ሲጠቀስ (ይህተግባር በእኔ እይታ ውግያ ተደረገበት ከሚባል ይልቅ "አብሼ የተታለለበትበመባል ሊጠቀስ ይገባል ነው የምለው።)
.
የጎጃሙ ራስ ደረሱ ጦቦ አብሼ ገርባን አታለው
ካሰሩት ቦሀላም አልሄድ ስላላቸው እንደ በሬ ቀንበር አንገቱ ላይ በማሰር እየጎተቱ ወደ ጎጃም ተወሰደ። (በሰላም ስም ይህን ሲያደርሱበት በእልህ የአንድ እጅ ጣቱን በእልህ እየነከሰ ከጥቅም ውጭ እንዳደረገ ጭምር ይነገራል)
.
አብሼን ጎጃም እንዳደረሱት የአከባቢው ገዢ የአዳል ተሰማ ሚስት ያን...ተዋጊ ሰራዊታቸውን የጨረሰ ሰው ለማየት እንዲያቀርቡላት ባዘዘችው መሰረት አቀረቡት።
ያ...የኦሮሞ ተዋጊ ሀይል አዛዥ በምግብ እጦት፣ቀንበር ተሸክሞ ለቀናት እንቅፋት እያላጋው ጎጃም የደረሰውን ወጣት መጎሳቆሉ መልከጥፉ አድርጎታልና መልከጥፉነቱን ገልጻ እንደሰደበችው የሰሙት የሆሮ ሴቶች እንዲህ በማለት ተረቱበት ይባላል..
.
Kan goduma keerra kan gowwumaa siin jette niitin Adaal Tasammaa በማለት የውስጥ ብግነታቸውን ተንፍሰዋል።
~(የሚያሳዝነው ደግሞ በወቅቱ የጎጃምን ጦር ሲመራ የነበረው አዳል ተሰማ ጭምር ማንነቱን ያጠፋ ግን ኦሮሞ የነበረ ነው)
~በመጨረሻም ያን ወጣት ጀበላ እና መጠራ በሚባል እስር ቤት ካሰሩት ቦሀላ በህይወት እንዳለ ከአንገቱ በታች ጉድጓድ በመቆፈር ቀብረውት ጸጉሩ ላይ ጨው በመነስነስ ፈረሶች በላዩ በመንዳት አስከፊ በሆነ መንገድ እንዲሞት አደረጉት...
.
አዎ ዛሬም በኦሮሞ ህዝብ ላይ ፍጅት እየፈጸሙ ያሉት
የራሳችን ቀዲዳ ወነቤዎች ከአብሼ ገርባ ገዳዮች ጋር ተባብረው ነው። by guma saqeta 23/08/2020 EC
إرسال تعليق
if you have any questions let me know